እራስን በራስ ያሳዬ ውይይት-በአያሌው አስረስ
ሃሳብን ስለመግለጥ የሚናገሩ በየቀኑ የምንገለገልባቸው ምሳሌዎች አሉ፡፡ አንዳንዶች መናገርን ግድ ሲያደርጉት ሌሎች አላስፈላጊ ያደርጉታል፡፡ ” ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል” የሚለው ምሳሌ፣ እያንዳንዳችን የልባችንን መሻት ሌላው ሰው ያውቅ ዘንድ፣ እኛም የእሱን ፍላጐት እንረዳ ዘንድ ምኖታችንን ፣አላማችንን መግለጥ እንዳለብን ያስገነዝበናል፡፡ ” ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባበትም” የሚለው ደግሞ የምትናገረው ነገር ሊያስከትል የሚችለው ጉዳይ አስቀድሞ ስለማይታወቅ አንድም ነገር መናገር […]