እራስን በራስ ያሳዬ ውይይት-በአያሌው አስረስ

ሃሳብን ስለመግለጥ የሚናገሩ በየቀኑ የምንገለገልባቸው ምሳሌዎች አሉ፡፡ አንዳንዶች መናገርን ግድ ሲያደርጉት ሌሎች አላስፈላጊ ያደርጉታል፡፡ ” ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል” የሚለው  ምሳሌ፣ እያንዳንዳችን የልባችንን መሻት ሌላው ሰው ያውቅ ዘንድ፣ እኛም የእሱን ፍላጐት እንረዳ ዘንድ ምኖታችንን ፣አላማችንን መግለጥ እንዳለብን ያስገነዝበናል፡፡

” ዝም  ባለ አፍ ዝምብ አይገባበትም” የሚለው ደግሞ የምትናገረው ነገር ሊያስከትል የሚችለው ጉዳይ አስቀድሞ ስለማይታወቅ አንድም ነገር መናገር የለብህም  ብሎ የሚገድብ ነው፡፡ ይህ የሀሳብ ነፃነትን ይገታል ብንል አልተሳሰትንም፡፡ ይሁን እንጂ ” ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል” በሚለው  ምሳሌያዊ አነጋገራችን ሥርዓት ያለው ሃሳብ አገላለጥ ዋጋ እንዳለው  ሰለሚነግረን በእርሱ እንጽናናለን፡፡

የአንድ አሳቢ ከመሆን ይልቅ የመናገርን፣ ሃሳብ የመለዋወጥን ፣ የመወያየት አስፈላጊነትንና  ጠቃሚነት የሚያም ነው ኢንሸቲቭ አፍሪካ ” በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የውይይት ባህልን ማስረጽ”   የሚል ፕሮጄክት ነድፎ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጄክቱ የሚካሄደው አዲስ አባባ ባለው የስዊንድን ኤምባሲ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን ፣የውይይት ፕሮግራሙ  ከሚካሄድባቸው ዩኒሸርስቲዎች ጋር በመሆን ዩዝ ኤንድ ካልቸር ዴቨሎፕሜንት ፋውንዴሽን የማስተባበር ሥራውን ይሠራል፡፡

በአምቦ  ዩኒቨርስቲ አስተዳደር የመሰብሰቢያ አድራሻ፣ ዩሸርስቲው ለውይይት በመረጣቸው የሴቶች እኩልነት ጥያቄ እና  ሥራዓተ ፆታ  እንዲሁም የበጐ ፈቃድ አገልግሎት  በሚሉ ሁለት ርዕሶች ላይ ሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ውይይቱ ተካሄዷል፡፡ የውይይቱ ተካፋዮች የዩኒሸርስቲው  ተማሪዎች፣ መምህራንና  የአስተዳደር ሠራተኞች ነበሩ፡፡

“የሴቶች የእኩልነት ጥያቄና ሥርዓተ ፆታ ” የሚለውን የመወያያ ርዕስ ያቀረቡት፣ በአምቦ ዩኒቨርስቲ የሕከምና ሳይንስ ኮሌጅ የድህረ ምርቃ ፕሮግራም  አስተባባሪ፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር  ሲስተር ሸዋዬ ፈጡማ ሲሆኑ፣  በእኩልነት ጥያቄው ላይ ብዥታ የሚፈጥሩ በርካታ ነገሮች መኖራቸውን ጠቁመው ሊለወጥ የማይችለው የተፈጥሮ ፆታ የችግሩ መደበቂያ እየሆነ ማገልገሉን በአፅንኦት  አስገንዝበዋል፡፡ የሴቶች ጥያቄ የፆታ ለውጥ ሳይሆን እኩል ድርሻ እኩል ተጠቃሚነት መሆኑን አስምረውበታል፡፡

በገጠር እናቶች በሴት ልጆቻቸው ላይ ሥራ ቢያበዙ ስለአላወቁ ነው ተብሎ ሊታለፍ ይችል ይሆናል፣ ሰልጥኖአል ተምሯል የምንለው የሕብረተሰብ ክፍል እራሱ ምን እየሠራ ነው? ብለው የሚጠይቁት ሲስተር ሸዋዬ፣ አባት ለልጆቹ መጫወቻ ሲገዛ ለወንድ ኳስ ለሴቷ የሕፃን አሸንጊሊት አደሚገዛ ዘርዘርው ሴት ልጁን ምን ጊዜም ለማታጣው  እናትንት እያዘጋጃት መሆኑን ልብ ልንል ይገባል ብለዋል፡፡

የሥርዐት ፆታ ዋና ጉዳይም ይህን በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ለሴትና ለወንድ የሚገባና የማይገባ የሚለውን  የተሳሳተ የሥራ ክፍፍል እንዲታረም ማድረግና ሴትም ሆነች ወድ ልጅ አኩል እንክብካቤ እዲያገኙ የሚደረግበት  ሥርዓት እንዲዘረጋ መሥራት መሆኑን አመልክተዋል፡፡

 

ወደ ዩኒሺርስቲ ለመግባትም ሆነ በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ለሴቶች የሚደረገው ድጋፍ ብቃት የሌላቸውን ተማሪዎች ለማብቃት ሳይሆን፣ መጀመሪያውኑ ብቃቱ  ኖሮአቸው እዚያ ደረጃ ላይ የደረሱ ሴት ልጆችን  የበለጠ ለማብቃት መሆኑ ግንዛቤ ማግኘት እንዳለበት ሲስተር ሸዋዬ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም በሥርዓተ ፆታ ተግባር ላይ ወንዶች እየሠሩ በሚገኙበት ጊዜ፣ እሱን ደግሞ በሴት ጉዳይ ምን አገባው የሚል ትችት እንደሚሰማ አውስተው፣ የሥርዓተ ፆታ ችግር ሕብረተሰቡ በረጅም ዘመኑ የገነባው ባህል በመሆኑ እሱን ለማስወገድ ደግሞ የውንዱም የሴቱም መተባበር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

እኛ ስለ እኩልነት እንናገራለን፤ የክርስትና ሃይማኖት ደግሞ ወንድ የሴት ራስ ነው ሚስት ለባሏ ትታዘዝ ወይም ትገዛ እያለ ያስተምራል፡፡ ከባህላችን  መሰረቶች አንዱ ደግሞ ሃይማኖት ነው፡፡ ይህን ተቃርኖ እንዲት መፍታት ይቻላል?  የሚል ጥያቄ የቀረቦላቸው ሲስተር ሸዋዬ ፣ ባለቤታቸው የእሳቸው ገዥ አለመሆናቸ  ውን፣ የሃይማኖት አባቶችም ሴትና ወንድ እኩል መሆናቸውን እያስተማሩ እንደሚገኙ ጠቁመው የአተያይና ያረዳድ  ችግር ሊኖር እንደሚችልም  እንደሚገነዘቡ አስረድተዋል፡፡

አቶ አብይ ወንድሜነህ ከሲቪክ የትምህርት ክፍል በአቀረቡት የመወያያ ሀሳብ በሀገራችን  ብልጭ ድርግም ከሚል  በቀር የቆየና ሥር የሠደደ የበጐ ፈቃድ አገልግሎት ባህል የሌለን መሆኑን ጠቁመው፣ መለመድ ያለበት፣ ሊለመድ የሚችል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ተማሪዎች በክረምት የእረፈት ጊዜያቸው ሕፃናትን እየሰበሰቡ መጽሐፍ ቢያነቡላቸው የንባብ ባህላችንን ለማሳደግ እንደሚያገለግሉ አሳውቀዋል፡፡

” የበጐ ፈቃድ አገልግሎት     በክፍያ የሚሰጥ አገልግሎት አይደለም፡፡ በምንሰጠው አገልግሎት ለሰው ልጅ ያለንን ክብር እናሳይበታለን፡፡ ይህን በማድረጋችን ደግሞ በገንዘብ የማይለካ የሕሊና እርካታ እናገኛለን” ያሉት አቶ አብይ በበጐ ፈቃድ ሊሰጥ የሚችለው አገልግሎት ይኸ ይኸ ተብሎ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አለመሆኑን አመልክተዋል፡፡

የተማሪዎች የበጐ ፈቃድ አገልግሎት በንጉሡ ዘመን በፊደል ሠራዊት ዘመቻ ተጀምሮ እንደነበር ያታወሱት አንድ  የውይይቱ ተሳታፊ በደርግ የተካሄማው የእድገት በሕብረት ዘመቻ ብዙዎችን የማንበብና የመጻፍ እውቀት እዳስጨበጠ አስረድተው ዛሬም ወጣቶች  ብዙ ሊሠሩበት እንደሚችሉ አስገንዘበዋል፡፡

ቀደም ሲልም የፕሮግራሙ አስተባባሪ የዩዝ ኤንድ ካልቸር ዴቨሎፕሜንት  ፋውንዴሽን ዳይሬክተርና የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ዜናዬነህ ግርማ፣ በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ለማምጣት ወጣቶች ከፍተኛ መስዋዕትነት መክፈላቸውን ዘርዝረው፣  አሁን አሁን በውይይት በመነጋገር ሊፈቱ የሚችሉ ጉዳዮች ሕይወት እሰከ ማሳጣት እየደረሱ በመሆኑ የመወያየት ልምድ  በከፍተኛ ተቋማት ሊጀመርና ሊዳብር እንደሚገባው  እስገንዘበዋል፡፡

መንግሥት  የሰላም ሚኒስቴር እንዲሁም  የሰላምና የእርቅ ኮሚሽን የሚባሉ  መሥሪያ ቤቶችን ማቋቋሙን ፣ አሥራ ሦስት  ሕጐች ማሻሻሉን  ጠቁመው፣ ብዙ ሊያወያዩና ሊያነጋግሩ የሚችሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ዛሬም  መኖራቸውን  አስረድተዋል፡፡

“በሀገራችን 108 የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ፡፡ አለማቸው ምን እንደሆነ ሲናገሩ አይሰማም፡፡ በፊት የመሪ ችግር ነበር አሁን ደግሞ የተመሪ  ችግር እየታየ ነው” ያሉት አቶ ዜናዬነህ  ተማሪዎች የውይይት ባህልን መገንባት እንዳለባቸው አሳውቀዋል፡፡

ተማሪ ፈንታዬነሽ ደመቀ በውይይቱ እራሷን ተምልሳ እንድታይ መገፋፋቷን  ጠቁማ በበጐ ፈቃደኛነት የአካባቢዋን  ሕብረተሰብ ለማገልገል ፍላጐት እንዳደረባት በሰጠችው አስተያየት አስረድታለች፡፡

አቅራቢና የውይይቱ ተሳታፊ  ሲስተር ሸዋዬ  የውይይቱን  ፋይዳ፤ “ወፍጮ ቤት የገባ ሰው ዱቄት ሳይቦንበት አይወጣም ፡፡ ማንም ባዶውን ተመልሷል ብዬ አላምንም ፡፡ እኔ እራሴ ብዙ አዳዲስ ሀሳቦች  ከውይይቱ አግኝቸበታለሁ” በማለት ገልጸውታል፡፡

ተማሪ ማሚቱ ይስሐቅ በበኩሏ ብዙ ልብ ያላቸቻቸዉን ጉዳዮች ልብ እንደትላቸው ስብሰባው ማድረጉን በመገረም ስሜት  አሰረድታለች፡፡ የሷ ወደራስ ተመልሶ ራስን የማየት የብዙዎች ተሰበሳቢዎች ስሜት እንደነበር  መረዳት አስቸጋሪ አልነበርም፡፡

ውይይቱን  ሁሉም ራሱን እንዲያይ ያደረገ ብሎ መግለጽ ይቻላል፡፡

ToR for Short term individual consultancy on the revision of School Violence Index (SVI)

TOR on SVI for a Consultant

Cartoon Series

#CivicEducation

Second youth discussion forum was held on Aug,17 at Dire Dawa university on the topic of relevance of College of Education the Context of Ethiopia, Dr. Daniel Mamo briefly discussed the major gaps concerning the education curriculum gap and how it should focus on the quality education.#CivicEducation #InitiativeAfrica  

 

Cartoon Story Series

British Council’s Active Citizen Training at Gebre Guracha

Initiative Africa with Shalom humanitarian Development Association is cascading the Activ citizen’s program funded by the British Council. This week, from August 15 – 18, 2019 will be at Gebre Guracha, Oromia Region. The program will be given to the micro small Enterprise groups and 2018+2019 graduates. Follow for more to come all over Ethiopia