የኢንሼቲቪ አፍሪካ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ
/0 Comments/in Uncategorized /by initiativeadminየሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አካል የሆነው ኢንሼቲቭ አፍሪካ አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም በሞዛይክ ሆቴል ተካሄዷል፡፡
ድርጅቱ እ.ኤ.አ በ 2020 ያከናወናቸው ስራዎች በሶስት መርሃ ግብሮች የተከፋፈሉ ሲሆን እነዚህም “ለውጥ በለውጥ – የስርዓተ ፆታ ጉዳዮችን ማካተት፣ በአካባቢ ልማት የወጣቶችን ልማት ማሳደግ እና የዜጎች ትምህርት እና የምርጫ ጉዳዮች እንዲሁም የንግድ ዘርፍ ማህበራት እና ምክር ቤቶችን መደገፍ እና አቅም ማጎልበት በተጨማሪም 14ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ስራዎች እንደሆኑ የድርጅቱ ጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅ አቶ የኋላሸት ገ/ሚካኤል ካቀረቡት ማብራሪያ መረዳት ተችሏል፡፡
ድርጅቱም በዚህ አመት ያጋጠሙት ችግሮች እና የተወሰዱ እርምጃዎችን ጊዜያዊ ሥራ አስኪያጁ ለጉባኤው አባላት ሲገልፁም ከመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ እና እርሱን ተከትሎ የተወሰደው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስብሰባን እና ተቀራርቦ መስራትን መከልከሉ የታቀዱ ተግባራት በመጓተታቸው ይህንንም ከድጋፍ ሰጪዎች ጋር በመነጋገር የእቅድ ክለሳ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡
አቶ የኋላሸት በማያያዝም ድርጅቱ ዓላማውን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት እንዲያስችለው ለተለያዩ ለጋሾች ያቀረበው የፕሮጀክት ፕሮፖዛል አዎንታዊ ምላሽ አለማግኘቱንም እንደችግር አስቀምጠዋል፡፡
ድርጅቱ እ.ኤ.አ በ2020 ላከናወናቸው ተግባራት በአጠቃላይ ከብር 18 ሚሊዮን 932 ሺህ ብር በላይ ወጪ ማድረጉን በውጭ ኦዲተር የተረጋገጠ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የፕሮግራም ወጪ 84 በመቶ፣ የአስተዳደራዊ ወጪ ደግሞ 16 በመቶ መሆኑን ከውጭ ኦዲተሩ ሪፖርት ማወቅ ተችሏል፡፡
ኢንሼቲቭ አፍሪካ እ.ኤ.አ በ2021 ዐም ያቀዳቸው ፕሮግራሞች የድርጅቱ ጊዜያዊ ስራ አስኪያጅ በዝርዝር ለማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት የገለፁ ሲሆን ከእነኚህም መካከል እ.ኤ.አ በ 2020 ያልተጠናቀቁትን ማጠናቀቅ በ ”ለውጥ በለውጥ – 2 የንግድ ማህበረሰብ ለሰላም” እና የዜጎች ትምህርት ጉዳዮች እንዲሁም በስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የመጀመሪያ ጊዜ መራጮች ትምህርት በተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ እና ዩኒቨርሲቲዎች መስጠት በተጨማሪም በተመረጡ ጉዳዮች የተለያዩ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ማወያየትም ሌላው የፕሮግራም ተግባር መሆኑ ታውቋል፡፡
የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት በቀረቡላቸው ሪፖርቶች እና እቅዶች ላይ አንዳንድ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ከጠየቁ በኋላ ባገኙት ምላሽ ረክተው ሪፖርቶቹን መሉ በሙሉ ተቀብለው አፅድቀዋል፡፡
Free Online Courses K-12
/0 Comments/in Uncategorized /by initiativeadminhttps://www.ixl.com/?partner=google&campaign=1748097747&adGroup=71330014267&gclid=Cj0KCQjwlN32BRCCARIsADZ-J4vlG3iy31QA5olQpqUyO-RGa9WrsiZ1JBnZtDqUauFz-KVQbiWWV9saAkOOEALw_wcB
This story is not Just An Australian story, it is the story of the whole cuntry
/0 Comments/in News, Uncategorized /by initiativeadminCOVID-19 Rapid Situational Assessment Update No.3
/0 Comments/in News, Uncategorized /by initiativeadminPROTECT YOURSELF FROM COVID-19 – ራስዎን ከኮሮና ቫይረስ ይጠብቁ
/1 Comment/in News, Uncategorized /by initiativeadmin
For further information please visit the Ethiopian Public Health Association Website /ለበለጠ መረጃ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ድህረ-ገጽ or Facebook page / የፌስቡክ ገጽ
or call on the Freeline – 8335
Upcoming Event – Life Skill Educational Theater
/0 Comments/in Uncategorized /by initiativeadminThe 3rd program for Life Skill Educational Theater program aiming to enhance Secondary School students awareness on their health is going to be presented today, 13th – Jan 2020 at Bole Secondary & Preparatory School at the students library in the mid-day at 12:30 p.m. (06:30 LT).
Everyone who is interested can attend the event and share their thoughts on the matter.
Upcoming Event – Life Skill Educational Theater
/0 Comments/in Uncategorized /by initiativeadminLife Skill Educational Theater program aiming to enhance Secondary School students awareness on various youth-related health concerns including SRH is being conducted in selected secondary schools in Addis Abeba.
The first segment of the training has been finished and performance of the theater by the students will begin from the coming Tuesday afternoon at Menelik II school. Everyone who is interested can attend the event and share their thoughts on the matter.
የሲዳማ ዞን ወደ ክልልነት መለወጥ ጥያቄ
/0 Comments/in Uncategorized /by initiativeadminየሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ታዛቢዎችን እንዲመድብ በጠየቀው መሰረት ኢኒሻኤቲቭ አፍሪካ፣ በህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም የሲዳማ ዞን ወደ ክልልነት መለወጥን ጥያቄ ስብሰባ ታድሟል።
Address
Cameroon Street, Lucky Bldg.
Tel: +251 116 622640 / 622641
Fax: +251 116 622642
Email: info@initiativeafrica.net
Office Hours:
Mon -Fri : 8.00Am – 5.30Pm