የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት – ሀገራዊ አንድነትን ለማጎልበት

በብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ላይ እየተሳተፉ ላሉ አካላት የ4 ቀናት ስልጠና በአዳማ ድሬ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡

ስልጠናው በብሔራዊ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት የተሻሻሉ ሞጅሎች/ኮርሶች ላይ የረዳት አመቻቾችና አስተባባሪዎችን አቅም ማሳደግ ላይ ያተኮረ ሲሆን ከስልጠናው አዲስ አበባ እና ድሬደዋ አስተዳደርን ጨምሮ ከ12 ክልሎች የተውጣጡ 114 ሰልጣኞችን በሁለት ቦታ በመክፈል ነው፡፡

መርሃ ግብሩ የተነደፈው ሀገራዊ አንድነትን ለማጎልበት፣ ሰላማዊ አብሮ መኖርን፣ ማህበራዊ ትስስርና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እንዲሁም ወጣቶችን በቁርጠኝነት፣ በተወዳዳሪነትና በስራ ፈጣሪነት አቅማቸውን በማጎልበት በኢትዮጵያ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት መሆኑን በእለቱ ተነግሯል፡፡

ፕሮግራሙ ለሰልጣኞች በምክንያታዊነት ማሰብና መኖር እንዲችሉ እንዲሁም የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት ውስጥ ሲሰማሩ ችግር መፍታትና የማሰብ፣ ራስን የማወቅና የግንኙነት ክህሎቶቻቸውን በማሳደግ በሀገረ መንግስት ግንባታ ያላቸውን ሚና እውቀትና ክህሎቶቻቸውን በመገንባት ላይ ዙሪያ ባጠነጠኑ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን በንግግር የዘጉት በኢፊድሪ በሰላም ሚኒስቴር የብሔራዊ ፈቃድና ማህበረሰብ አገልግሎት የክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሙለታ ሲሆኑ እሳቸውም ሰልጣኞች ወደ የአካባቢያቸው ሲመለሱ ያገኙትን እውቀት ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን  ብዙ ወጣቶችን በማስተባበርና በማፍራት አሰልጥኖ ማብቃት ላይ ያተኮረ ተግባር ማከናወን እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ስለስልጠናው አጠቃላይ ሁኔታ የአንዳንድ ሰልጣኞችን አስተያየት ለመቃኘት ሞክረናል፡፡ በቅድሚያ ወጣት ካህመር ታዬን አስተያየት ነበር የተቀበልነው፡፡ ወጣቱ የመጣው ከሲዳማ ክልል ይርጋለም ዞን ሲሆን እሱም “ስልጠናው ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር መነቃቃትን ፈጥሮልናል” ብሏል፡፡ ሌላው አስተያት ሰጪ ወ/ሪት ደበሌ አያና ትባላለች፡፡ የባሌ ሮቤ ዞን ሰላም አስተባባሪ ስትሆን “በዚህ ስልጠና ስሳተፍ የመጀመሪያ ጊዜዬ ነው፡፡ ስልጠናው ጊዜ አጭር ቢሆንም በስልጠናው ብዙ እውቀት አግኝቼበታለሁ፡፡ ከነበረኝ አስተሳሰብ ከፍ እንድል አድርጎልኛል፡፡ ይህ ስልጠና ጊዜ ተሰጥቶት ተከታታይነት ባለው መልኩ ቢደረግ ይመረጣል” ስትል ገልፃለች፡፡

ወርቅነህ መራ የተባለው የጎንደር ሰላም አስተባባሪ ደግሞ ስልጠናውን ስሳተፍ የመጀመሪያ ጊዜዬ ቢሆንም “በዚህ ስልጠና ከተለያዩ የአገራችን ክልሎች የመጡ ወጣቶችን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ያሳተፈ በመሆኑ እርስ በእርስ እንድንነጋገር ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የጋራ ሀሳብ እንድንይዝ አድርጎናል፡፡ ስልጠናውም አሁን ካለን አስተሳሰብ አሻግረን እንድናይ ያስቻለን ነው” ሲል ተናግሯል፡፡

ይህ ስልጠና የተካሄደው ኢኒሺየቲቭ አፍሪካ ከኢፌድሪ ሰላም ሚኒስቴር እና ብሪትሽ ካውንስል ጋር በመተባበር መሆኑ ታውቋል፡፡

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *