በመቀሌ የፕሮጀክት ስምምነት ፊርማ ተካሄደ

በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበው ኢንሼቲቭ አፍሪካ ከማላላ ፈንድ በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት  በትምህርት ወደ ኋላ የቀሩ ተማሪዎች በተለይም ልጃገረዶችን የተፋጠነ ትምህርት እንዲያገኙ የማስቻል የ3 ዓመት የፕሮጀክት ስምምነት ፊርማ ስነስርአት ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ተካሄደ።

ከፕሮጀክቱ ዋነኛ ተግባራት መካከል እድሚያቸው ከ9 እስከ 15  አመት ለሚሆኑ 1000 ተማሪዎች በማህበረሰብ አቀፍ የተፋጠነ የትምህርትና የመምህራን ስልጠና መርሀ-ግብሮች መተግበር እንዲሁም የህይወትና ክህሎት  ስልጠና እንዲያገኙ ማስቻል ሲሆን ፕሮጀክቱ የሚተገበረው በማዐከላዊና በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞኖች ባሉ 6 ወረዳዎች ነው።

የፕረጀክት ስምምነት ፊርማው የተካሄደው ኢኒሺዬቲቭ አፍሪካ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ እና  እቅድ ፋይናንስና እርዳታ ማስተባበሪያ  ቢሮ ጋር ነው።

በፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት ሁለቱም የሴክትር መስሪያ ቤቶች ተወካዮች ኢንሼቲቭ አፍሪካ በክልሉ በጦርነት የተጎዱ ወጣት ሴቶችና ወንድ ልጆች በተፋጠነ ትምህርት ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ለመተግበር በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑ የሚያስመሰግነው ነው ካሉ በኋላ ፕሮጀክቱ ስኬታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።   

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *