On the occasion of the launching of the 50:50 program, The executive director of Initiative Africa, Mr.Kebour Ghenna, cordially invites you to a cocktail party at the Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa.
Consultative workshop with school leaders
/26 Comments/in Uncategorized /by initiativeadminIA hosted a consultative workshop with school leaders in Addis Ababa on Gender Equality: “Making Change Happen” project. The project focuses on gender empowerment programs, which address social norms and behavior change, seek out and build partnerships among organizations that work on gender issues, and develop programs that involve men and boys in the promotion of gender equality.
We will be having a consultative workshop with school leaders in Addis Ababa on “Gender Equality: Making Change Happen” project. The project focuses on gender empowerment programs which address social norms and behavior change, seek out and build partnerships among organizations that work on gender issues, and develop programs that involve men and boys in the promotion of gender equality.
ጩህ ጩህ አለኝ
/1 Comment/in Uncategorized /by initiativeadmin አያሌው አስረስ
(ለኢኒሺየተቭ አፍሪካ የቀረበ)
መስቀል አደባባይ አጠገብ በሚገኘው አዲስ አበባ ሙዝየም ውስጥ ሰሞኑን አንድ አውደ ትርኢት ቀርቦ ነበር፡፡ አውደ ትርኢቱን ያዘጋጁት ሴታዊት የሚባል መንግሥተዊ ያልሆነ ድርጅት, ከዩኔ ውመን እና የስዊዲን ኤምባሲ (Sweden Embassy) በጋራ በመሆን ነው፡፡ ‹‹ ምን ለብሳ ነበር? ›› በሚል ርእስ የቀረበው ይህ አውደ ርእይ ያተኮረው አለባበስን ተንተርሶ በሴቶች ልጆች ላይ የተፈጸመውን የወሲብ ጥቃት በማሳየት ላይ ነው፡፡እኛ ደግሞ ጾታ እንጂ አለባበስ የመደፈር ምክንያት አይደለም፤ ያ ቢሆን ኑሮማ የአለቀ የተማሪ የደምብ ልብስ (ዩኒፎርም ) የለበሰቸው መክሊት በምን ምክንያት ትደፈራለች? ብለን እንሞግታለን:: ፊት ለፊት አያምጡት እንጂ የእነሱም መሻት ይህን መስረገጥ ነው፡፡
ጥቃቱ የተፈጸመባቸውን ልጆች በእድሜ ስናይ ደግሞ የሰባት አመቷን አሚናን እና የአስራ ዘጠኝ አመቷን መንበረን እናገኛልን፡፡ጥቃቱ የደረሰባቸው 16 ሴቶች ሲሆኑ ጥቃት አድራሽ ወንዶች ደግሞ 17 ናቸው፡፡ ይህ ማለት አንደኛዋ በሁለት ወንዶች ተደፍራለች ማለት ነው፡፡ ጥቀቱን ከፈጸሙት 17 ወንዶች ለሕግ የቀረቡት ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ በሕግ ቁጥጥር ሥር ገብቶ የነበርው ሶስተኛው አጥቂ ለፖሊስ ጉቦ ሰጥቶ መውጣቱና መልሶም አለመያዙ ተገልጧል፡፡ አራተኛው ደግሞ በዋስ ወጥቶ በዚያው ጠፍቷል፡፡
የመደፈር አደጋ ከደረሰባቸው ውስጥ አንዷ ኮከብ የተደፈረቸው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ነው፤እስረኛ ሆና ተገኝታ አይደለም ሕግ የጠብቀኛል ብላ ገብታ እንጂ፡፡ ከታሪኩ የድርጊቱን አፈጻጻም መገመት ይቻላል፡፡ ኮከብ ከመኖሪያዋ ብዙም ወደ ማታውቀው አካባቢ ርቃ ሔዳለች፡፡ ልትመለስ ስታሰብ ጊዜው መሽቷል፡፡ በዚያ የምታውቀው ያሳድረኛል የምትለው ሰው ወይም ዘመድ የላትም፡፡ ስለዚህም ፖሊስ ጣቢያ ተጠግታ አድራ በሰላም ወደ አካበቢዋ ለመመለስ ወስና ጣቢያ ትሔዳለች፡፡ በቦታው የነበሩት ፖሊሶች በሃሰቧ ተስማምተው ከሴት እስረኞች ጋር እንድታድርና ጠዋት ወደ አገሯ እንድትሔድ ይወሰናሉ፡፡ ተረኛ ፖሊሱ ግን ወስዶ ከሴት እስረኞች ጋር እንድታድር አላደረገም፡፡ ከእረሱ ጋር እንድታድር አድርጎ ደፈራት፡፡ ጠዋት ላይ ወስዶ ከሴት እስረኞች ጋር ሲቀላቅላት እስረኞች ተቀወሙ፡፡ ስለዚህም ወንጀሉ ተጋለጠ፡፡ ምን ያደርጋል እሱም ለሕግ አልቀረበም፡፡ጩህ ጩህ የአለኝ ለዚህ ነው፡፡
በአክሰትና ባጎት እጅ አድገው ለቁም ነገር የደረሱ ብዙዎች ቢኖሩም የቤዛዊት እጣ ግን ያማል፡፡ ‹‹ መጣችልህ የፈለግከውን አድረጋት›› ብላ አሳለፋ ለደፋሪው የሰጠቻት ወገኔ ብላ የተጠጋቻት እንደ አንድ የቤት ሠራተኛ አገልጋይዋ አድርጋ ጉለበቷን ሰትበዘብዛት የነበረችው አክስቷ ናት፡፡ የሰባት አመቷ የአሚና እና የአስራ ስምነት አመቷ የአርሴማ ጥቃት ደግሞ ለመናገር እራሱ ይከብዳል፡፡ ሰው ከሰውነት ወርዶ ፍጹም እንስሳ ሆኖ በእንስሳነት በሕሪውና ተግባሩ የተገለጠበት ድርጊት ነው፡፡ አርሞ ኮትኩቶ ለቁም ነገር ማድረስ የነበረበትን አባት የገዛ ልጁን ሲደፍር በምን ቃል ምሬትንና ጥላቻን መግለጥ ይቻላል ? የክርሰትናና የእስልምና ወይም የሌላ እምነት ተከታይ ሃይማኖተኛ ሕዝቦች ነን የምንል ሰዎች የሞራል ልዕልናችን ወደ የት አለ? ብሎ መጠየቅ ግድ ይሆናል፡፡ይህ አይነቱ ቅሌትና የሞራል ዝቅጠት አያሰጮህም?
በመጠቃተቸው የደረሰባቸው ጉዳት ሳያንሰ አንዳንዶቹ ለማርገዝና ለመውለድ ተገድደዋል፡፡አክስቷ ለመደፈር የዳረገቻት ቤዛዊት ልጇን ለማየት ምን ያህል ትጠላ እንደነበር የምተናገረው ምርር ባለ ቃል ነው፡፡ መከራውንና የመከራውን ማስተወሻ በአንድነት ለመያዝ መገደድ እሷን አታድርገኝ ያሰኛል፡፡
ጥፋቱ እንደተራ ጉደይ ታይቶ ፋይሉ የትም ተጥሎ ይሆናል፡፡ ተበዳዮች ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተመላልሰው ነገሩን ለመቀስቀስ ሲነሱ ምን እንደሚጠብቀቸው ኤተወቅም፡፡ ምን አልባት መጠቋቆሚያም እየተደረጉ እየተሸማቀቁ ተጨማሪ ጉዳት ላለማስተናገድ ቢቀርስ ብለው ነገሩን ትተውት ሸሽተው ቤታቸው ገብተው ዘግተውም ይሆናል፡፡መጮህ አሁንም መጮህ የሚያስፈልገው በሕገ አስፈጻሚው ላይ ነው ፡፡ ‘እነእከሌ ምን ሆኑ’ የሚሉ ተጨማሪ ጥቃት ፈጻሚዎች እያበዛብን እንዳይሆን ያሰጋል። ሁሉም ወገን በህፃናትና ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት ለመከላከል ዘብ ሊቆም ይገባል። በተለይ በት/ቤቶችና በማህበረሰቡ ውስጥ የባህርይ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ከተቋቋሙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር መተባበር ያስፈልጋል።
#PhysicalBullying #AntiBullyingweek #ChooseRespect #MakeChangeHappen #InitiativeAfrica
/0 Comments/in Uncategorized /by initiativeadmin#PhysicalBullying is using one’s body and physical bodily acts to exert #power over peers it includes Punching, kicking and other #physicalAttack. #AntiBullyingweek #ChooseRespect#MakeChangeHappen #InitiativeAfrica– join us and share this post to take a stand against bullying.
#AntiBullyingweek #ChooseRespect #MakeChangeHappen
/0 Comments/in Uncategorized /by initiativeadmin#AntiBullyingweek
It’s #AntiBullyingweek with a theme of #ChooseRespect join our campaign and to #MakeChangeHappen #share this post to take a #stand_against_bullying #InitiativeAfrica.
People under 25 will, at some point, experience bullying. As a result, 1 in 3 will #selfHarm, #grades_drop, will experience #socialanxiety, #undermined_selfesteem, and #depression.
This year we are using #AntiBullyingWeek to encourage people to #SpeakUp about bullying by having an #EssayWritingContest in schools all over #AddisAbaba.
#TypesOfBullying #ChooseRespect #MakingChangeHappen
/0 Comments/in Uncategorized /by initiativeadmin#TypesOfBullying #ChooseRespect #MakingChangeHappen
#Physical_bullying includes hitting, kicking, tripping, pinching and pushing or damaging property. …
#Verbal_bullying includes name calling, insults, teasing, intimidation, homophobic or racist remarks…
#Emotional_bullying includes harassment, disrespect,mistreat, hostility…
#Cyber_bullying Stalking, Hacking accounts, hate messages, anonymous threats ..
Address
Cameroon Street, Lucky Bldg.
Tel: +251 116 622640 / 622641
Fax: +251 116 622642
Email: info@initiativeafrica.net
Office Hours:
Mon -Fri : 8.00Am – 5.30Pm